የልጆቻችን የአእምሮ ጤንነት

 የልጆቻችን የአእምሮ ጤንነት

ልጆችዎን ወይም በቤተስብዎ ውስጥ ያሉ ወጣቶችን ስለሚገጥማቸው ችግሮች እያነሱ በመነጋገርና  መፍትሔውን አብሮ ለመፈለግ አስፈላጊውን  ድጋፍና ማበረታቻ እየሰጡ ደስተኛና  የተሟላ  ህይወት እንዲኖሩ ማድረግ ይችላሉ። ይህ ጽሁፍ አንዳንድ የችግሮች መንስኤ ምልክቶችን ለይተው እንዲያውቁ፤ ቶሎ እርዳታ ለማግኘት መሞከርና እርስዎም ልጆችዎን እንዴት ማገዝ እንደሚችሉ ያሉትን መንገዶች በማሳየት ይረዳዎታል።

ወላጆችም ሆኑ ቤተሰቦች ምን ማድረግ ይችላሉ? 

የቤተሰቡ አካል መሆንና በጥሩ ሁኔታ ማሳደግ ለልጆችና ለወጣቶች የአእምሮ ጤነነትና ደህንነት በጣም አስፈላጊ ነው።

አያውቁት እንደሆን እንጂ የልጆችዎን የአእምሮ ጤንነት በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊጠብቁ ይችላሉ፡

1.  ለልጆችዎ ያልዎትን ፍቅር፤ ፍላጎትና ለደህንነታቸው የሚሰጡት ጥንቃቄ

2.  ልጆችዎ ስለሚገጥማቸው ችግሮች እንዲያወሩ እና  ምንም እንኳን ከባድ የሆነ ቢሆንም መፍትሔዎችም በጋራ እንዲሹ ማበረታታት

3.  በጭንቀት ውስጥ ወይም አእምሮን  የሚረብሽ  ሁኔታ ሲገጥማቸው ልጆችዎን  መንከባከብ፡

4.  ከልጆችዎ ጋር አብረው ጊዜ ማሳለፍ፤እቅዶችን እያወጡ ነገሮችን ተባብሮ መስራት

5.  በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮችና የሚያሳዩትን ለውጦች መገንዘብ፡

6.  አንድ ወጥ የሆነ እንክብካቤ መስጠትና ግብታዊና መጥፎ  ቅጣት አለመስጠት፡፡

7.  ለእያንዳንዱ  ልጆችዎ በተናጠል ጊዜ እየሰጡ አንድ ላይ ማሳለፍ እና

8.  ልጆችዎን እናንተ በምትፈጥሩት  ጭቅጭቅ ውስጥ እንዲዘፈቁ ከማድረግ መቆጠብና በቤተስብ አባላት መካከል አለመግባባት ቢነሳ መፍትሔ መስጠት ካልተቻለ ደግሞ አስቸኳይ አርዳታ መሻት ያስፈልጋል።

ስሜታቸውን ለመቆጣጠር ወይም የአእምሮ ጤንነት ችግር ያለባቸውን ልጆችም ሆኑ ወጣቶችን መርዳት የሚቻለው መጀመሪያ በእርጋታ በማዳመጥ ነው። መቀበልና አጋር ሆኖ መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው። ልጆችዎ ለሚያምኑት ሰው ችግራቸውን እንዲያካፍሉ ማበረታታትና እርሶም ለማዳመጥ ዝግጁ ሆነው መገኘት፤ ካልፈለጉ ችግራቸውን እንዲናገሩ ግን ማስገደድ የለብዎትም። ልጆች ጥሩ ሲሰሩ በውጤታቸው ሁሉ ያመስግኗቸው በተለይም አንስተኛ የሆኑትን። ድክመታቸውን ግን በማንሳት ወቀሳ ከማድረግ መቆጠብ።

ልጆችው ከሰው ጋር መሆን ወይም ለብቻቸው መሆን የሚገባቸውን ጊዜ በመመካከር መሰራትና ጥቅም የሚያገኙባቸውንና የሚያስደስታቸውን ነገሮች ተባብሮ በጋራ ማከናውን፡፡

እራስዎትንም  ሳይዘነጉና ሲያስፈልግዎትም እርዳታ ከመጠየቅ ወደኋላ እንዳይሉ።

ወጣት ልጆች ለስሜት መለዋወጣቸውና ለአእምሮ ጤንነት ችግሮቻቸው የህክምና እርዳታ በሚያገኙበት  ወቅት የእርስዎ እገዛ ንዲያገግሙ ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ስለደህነነታቸው እንደሚያስቡና በማናቸውም ጊዜ አብረዋቸው እንደሆኑ በመግለጽ ወጣቶችን መርዳት ይችላሉ። በቤት ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታን መፍጠርና በቤተሰብ መሐል የሚነሱ ግጭቶችን መቀነስ፤ ጤናማ የሆኑ ምግቦችን ማቅረብ፤ ልጆችዎ የሚያስደስታቸው ነገሮችን እንዲሰሩ ማበረታታትና እራሳቸውን ሊጎዱበት ይችላሉ የሚሏቸውን ነገሮች በሙሉ ከአካባቢው ማስወገድ።

አንዳንድ ወጣቶች የሚሰጣቸውን አርዳታ አንፈልግም ብለው ሊከላከሉ ወይም ምንም ዓይነት ችግር የለንም ሊሉ ይችላሉ። ይህ ሲሆን አርስዎ እራስዎ እርዳታ መፈለግ ይኖርብዎታል። ነገሩ አሳሳቢ ሆኖ ሲገኝ በአስቸኳይ እርዳታ ማግኘት ይገባል። ይህ እንግዲህ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ጉዳዩ ምንም እንኳን ሚስጥር ቢሆንም ለሌሎች ለመግለጽ ግድ ይሆንብዎታል።


Comments

Popular posts from this blog

ብሩህ ተማሪ