ብሩህ ተማሪ

 የፕሮጀክቱ ዋና ግብ

2016 2017 እና 2018 . የትምርት ዘመናት በመላው አማራ ክልል ሁለተኛ ደረጃ አስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ ለሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ 20 ከመቶ ለሚሆኑት የሁለት ዙር የሁለንተናዊ ብርታትና መንፈሰ ጠንካራነት፣ የሰብዕና ልማት፣ የመማር ስነዘዴና የዓለማቀፋዊ ተማሪነት እሳቤ ስልጠናዎችንና ልምምድ ጥቅሎችን በመስጠትና የአንድ ወር ድጋፍና ክትትል እገዛዎችን ማድረግ አዎንታዊ የአመለካከትና እይታ ለውጥ ሁለንተናዊ የሰብዕና መነቃቃትንና የዳበረ የህይወት ክህሎትን በመፍጠር ራሳቸውን እንዲያሻሽሉና በትምህርታዊ ስኬት እንዲያድጉ ማስቻል፡፡

የሚጠበቅ ተጽዕኖ

·         ከዚህ በፊት ከነበራቸው እይታ የሰፋ ዓለማቀፋዊ ማይንድሴት፣ ፈጣሪነትና አዳዲስ ነገሮችን ማምጣት እንደችሉ፣ ከምንም በላይ ለሙያቸውና ለትምህርታቸው የተነሳሱና ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ይሆናሉ፤

·         የራሳቸውን መክሊትና ልዩ ተሰጥኦ እንዲረዱ፣ ከአሁኑም የህይወታቸውን ዓላማ እንዲለዩና መምህራን አገልግሎታቸውን ተማሪዎችም የሚማሩትን ትምህርት ለምን ዓላማ እንደሚያውሉት እውቀትንና መረዳትን ያዳብራሉ።

·         ለጊዜያዊ ደስታዎችና ጨዋታዎች የሚያውሉትን ውድ ጊዜያቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙ ለዓላማቸው ስኬት መንገድን ይጀምራሉ፡፡

·         የግለሰብን ሰብዕናቸውን በማልማት፣ ራስን መግዛትና የህይወት ክህሎቶችን መገንዘብ ለህይወት ምን ያክል እንደሚጠቅም ተረድተው በመርሐግርብር የሚኖሩ ታታሪ ግለሰቦች ይሆናሉ፡፡

·         ብሩህ ተስፋ ሰንቀው ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው፣ ለአካባቢያቸው፣ ለሀገርና ለዓለም ምን እንደሚያበረክቱ በማለም ራሳቸውን ትልቅ አድርገው እንዲረዱና እንዲኖሩ ይሆናሉ፡፡

የፕሮጀክቱ አተገባበር

'ብሩህ ተማሪ' ፕሮጀክት የመፈጸሚያ ጊዜ

የመጀመሪያ ምዕራፍ ከሰኔ 2016-ጥቅምት 2017 .

ሁለተኛ ምዕራፍ ከጥቅምት 2017 . ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2018 .

ሶስተኛ ምዕራፍ ከጥቅምት 2018 . ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2019 .

የመፈጸሚያ ቦታ

ይህ ስልጠና በአማራ ክልል ውስጥ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ለመስጠትና በቀጣይ ሶስት ዓመታት ውስጥ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎችን በክልላችን ለማሰልጠን የታሰበው የናዳን ኢኒሼቲቭ አንዱ አካል ሲሆን አሁን ላይ በባህርዳር ከተማና አካባቢዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ፓይለት ተደርጎ ውጤታማነቱ ክጅምሩ እየታየ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ከክልሉ ትምህርት ቢሮና ከከተማ አስተዳደሩ የሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበር የሚሰራ ነው፡፡ በዚህ የትብብር ስራም የማሰልጠኛ ቦታ በየትምህርት ቤቶች የላይበራሪ/ የመማሪያ ክፍሎች ስልጠናውን ለመስጠት ታስቧል፡፡

የጥቅሉ አሰጣጥ ዘዴዎች

ይህ በጥልቅ ይዘት የተዘጋጀ የአስራ ሁለት ሰዓታት የገጽ ለገጽ (Face to Face) የስልጠና ጊዜንና አስር ሰዓታት የልምምድ ጊዜን የሚወስድ ሲሆን ለተሳታፊዉ በሚመደብለት የግል አሰልጣኝ ባለሙያ (Personal Coach) ለአራት ተከታታይ ጊዜያት በየሳምንቱ አንድ ቀን በአካል በሚደረግ የሜንቶርሺፕና ኮቺንግ ግንኙነት የተሳታፊው እውነተኛ ልምምድ እየተገመገመና እየታገዘ በግሉ ራሱን እንዲያሻሽል፣ እንዲሁም በተሳታፊው ፍላጎት መሰረት በግሉ የወደፊት ዝንባሌ ላይ መሪና አማካሪ ባለሙያ (Mentor) ተመድቦለት የህይወቱን ግቦች (Personal and Professional Life Goals) በቶሎ እንዲያሳካና ሁለንተናዊ በጎ ለውጥንና እድገትን ማስገኘት የሚያስችል ድጋፍና ክትትል አለው፡፡

የሚወስደው ሰዓት

36 ሰዓት (36 hours) - 12 ሰዓት የገጽ ለገጽ (Face to Face) 10 ሰዓት የግል ድጋፋዊ ልምምድ፣ ቀሪው 14 ሰዓት የክትትልና ግምገማ የቤት ልምምድ፡፡

ተማሪ ነህ? ተማሪ ነሽ? ወይም ተማሪ ልጅ፣ እህት፣ ወንድም ወይም ጓደኛ አለዎት?

🌻🌻እንኳን ደስ አላችሁ🌻🌻

እንግዲያውስ ብሩህ ተማሪ ፕሮጀክትን ይወቁት፤


ይህ ብሩህ ተማሪ የተሰኘ ፕሮጀክት ጥናታዊ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ ናዳን ኢኒሼቲቭ በተማሪዎች ላይ አዎንታዊ ለውጥን ለትምህርት ቤቶቻችን የማይቀለበስ ሽግግርን ለማስገኘት የተዘጋጀ ፕሮጀክት ነው፡፡ ከአሁን ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቀጥሎም በክልሉ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ከአሁናዊ አካላዊ፣ ስነልቦናዊና የመንፈስ ተግዳሮታዊ ጫናዎች እንድናልፍ፣ ሁለንተናዊ መልካም የሰብዕና ልማትና መነቃቃትን፣ 

ለትምህርትና ለፈጠራ መነሳሳትና መትጋትን፣ ዘመኑን መዋጀትን፣ አሻግሮ የወደፊቱን ማየትን፣ ሀገራዊ ክብርና እሴትን በማንገብ ለለውጥ ዝግጅትንና የአሁኑን የዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ተማሪነት ማይንድሴትን የሚያላብሱ የስልጠና፣ ልምምድና ክትትል ጥቅሎችን የያዘ ጥልቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ አራት ክፍላተ አርዕስቶችን (Modules) የያዘ ሲሆን ለሁሉም የስልጠና፣ የልምምድ፣ የድጋፍና የክትትል ጊዜ የተመደበና በእያንዳንዱ ሞጁል ላይ እውነተኛ የባህሪና የልቦና ውቅር ለውጥን (habits and paradigm shift) እንድናገኝ የሚረዱ የልምምድ ቅጾች (Templates, Workbooks) ተካተውበታል፡፡  


👉ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ላሉ ተማሪዎች ሁሉ እንደየ እድሜያቸውና፣ እንደየትምህርት ዝግጅታቸው የተዘጋጀ ልዩ የትምህርትና የሁለንተና ህይወትን የሚቀይር ፕሮጀክት።


የ"ብሩህ ተማሪ" ፕሮጀክት የመጀመሪያው ዙር 400 ተማሪዎችን ተቀብለን በልህቀት በማሰልጠን አሁን ላይ ሶስተኛውን የኮቺንግ መርሐግብራችንን ጨርሰን የአራተኛውን ሳምንት ኮቺንግና ሜንቶርሺፕ መርሐግብር እያስኬድን ነው። 


🛎🛎 ሁለተኛው ዙር ምዝገባ እየተካሄደ ነው👩‍💻👨‍💻

🤝አሁኑኑ ይደውሉ ወይም ቢሮ ይምጡና ይመዝገቡ ይቀላቀሉን!🤝


በፕሮጀክቱ፥

👉👉የአንድ ቀን የሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የአንድላይ ልዩ ስልጠና፤

👉👉የአራት ሳምንታት ልዩ የግል ድጋፍና ክትትል (ኮቺንግ እና ሜንተሪንግ) መርሐግብር ከብቁ የግል አሰልጣኝና አማካሪዎ ጋር (Exclusively with Your Personal Coach and Mentor)!


👉ሁለተኛው ዙር የባህር ዳር ብሩህ ተማሪ ፕሮጀክት ቅዳሜ በ20/11/16 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00-10:30 ባህርዳር ቀበሌ 4 ለምለሚቱ የገበያ ማዕከል ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ባለው የናዳን የስልጠና ልህቀት ማዕከል የሚካሄድ ሲሆን የሜንተርሺፕና ኮቺንግ መርሐግብሩ ደግሞ ቀጥሎ ባሉት አራት ተከታታይ ሳምንታት በየአቅራቢያችሁ ባሉ አራት ማዕከሎቻችን ላይ የሚሰጥ ይሆናል።

✍️ምድብ አንድ: ቀበሌ 13 SOS Compound 

✍️ምድብ ሁለት: ቀበሌ 15 ኖክ ላይ እሸት አካዳሚ ግቢ ውስጥ

✍️ምድብ ሶስት: ቀበሌ 4 በናዳን የስልጠና ልህቀት ማዕከል

✍️ምድብ አራት: አባይ ማዶ ቀበሌ 11 በናዳን ኢኒሼቲቭ ቅርንጫፍ ቢሮ


🌻🌻 ይመዝገቡ ከሁሉም ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር ይገናኙ፣ ራስዎን ያሳድጉ፣ ጫናዎችን ያሸንፉ፣ ዓለማቀፍ ተማሪ ይሁኑ!🌻🌻

🗣ሁለተኛው ዙር የባህርዳር ብሩህ ተማሪ ስልጠናና ልምምድ ቅዳሜ በ20/11/16 ይጀምራል።



















Comments

Popular posts from this blog

የልጆቻችን የአእምሮ ጤንነት