ብሩህ ተማሪ
ይህ ‹‹ብሩህ ተማሪ›› የተሰኘ ፕሮጀክት በናዳን የልህቀት ማዕከል የማህበራዊ፣ ስነ ልቦና፣ ጤና እና የስራ አመራር ጉዳዮች ስልጠና፣ ጥናት፣ ምርምር፣ ልማትና ማማከር አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋም የተዘጋጀ ፕሮጀክት ነው፡፡ ብሩህ ተማሪ ፕሮጀክት ጥናታዊ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ ናዳን ኢኒሼቲቭ የትውልድ ትንሳኤን በመሻት የተለያዩ አጋር አካላትን፣ በርካታ ብቃት ያላቸው አሰልጣኝ አማካሪዎችን፣ የስነባህሪና የአእምሮ ሀኪሞችን፣ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ አማካሪዎችን በማስተባበር ለአንድ ዓመት ተደክሞበት በተማሪዎችና መምህራን ላይ አዎንታዊ ለውጥን ለትምህርት ቤቶቻችን የማይቀለበስ ሽግግርን ለማስገኘት የተዘጋጀ ፕሮጀክት ነው፡፡
ከአሁን ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቀጥሎም በክልሉ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉ የሚተገበር ይህ ፕሮጀክት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከትምህርት ጋር የሚስተዋሉና በስፋት የሚነሱ ችግሮችን ከታች ወደላይ ለመፍታት ያለመ አሁን ላይ ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ተስፋ ማጣት፣ ለትምህርት ትኩረት ያለመስጠትና መሰል ችግሮችን፣ መምህራንም ከሙያዊ ክብር፣ ቀጣይነነት ካለው የሙያዊ ክህሎት እድገት ትኩረት ያለመስጠትና መሰል በጥናት ለተገኙ ችግሮች አይነተኛ መፍትሔ ይዞ የመጣ ተግባራዊ ፕሮጀክት ነው፡፡
Comments
Post a Comment