የ''ያ ጊዜ አሁን ነው!" ፕሮጀክት ጣና ክፍለ ከተማ

November 2022 - ህዳር 2015 ዓ.

ተቋማት ለተለሙት ዓላማ፣ ላዩት ርዕይ፣ ላሰቡት ግብና ለሚናፍቁት እድገት ቁመና እንዲኖራቸው፤ ግለሰቦች በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ መንፈሳዊ፣ አካላዊ፣ አእምሮአዊና ስነ ልቦናዊ ህይወታቸው ጤናማ እንዲሆኑ ናዳን ወደ ተፈጥሮአዊ ኃያልነት፣ ወደ ራዕይና ምናባዊ ህይወትዎ እንዲጓዙ ሊረዳዎት መጥቷል፡፡

በባህርዳር ጣና ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች ስንሰጥ የነበረውን የራስን ማበልጸግ፣ ስብዕና እድገት፣ ዓላማ መር ህይወትና የራስዎን ስራ ይጀምሩ ጥቅል ስልጠናና ልምምድ ዛሬ በስኬት አጠናቀናል፡፡ ይህ በናዳን የተዘጋጀው የ''ያ ጊዜ አሁን ነው!" ፕሮጀክት አካል ነው፡፡ ለዚህ የስልጠና መሳካት በጎ ተጽዕኖ ላደረጋችሁት ሰልጣኞች፣ ሽምብጥ የወጣቶች ማዕከል፣ ዮፍታሔ መጻህፍት መደብርና የጣና ክፍለ ከተማ ማህበራዊ ዘርፍ ሰራተኞችና የሁሉም ቀበሌዎች አስተባባሪዎች ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡

የናዳን የአመራርና አሰልጣኞች ቡድን (NADAN TEAM) ዛሬም ደስ በሚል ጥምረትና መስተጋብር ሁሉ ነገር ያማረና ሸጋ እንዲሆን አድርጓል፡፡






Comments

Popular posts from this blog

ብሩህ ተማሪ

የልጆቻችን የአእምሮ ጤንነት