ያ ጊዜ አሁን ነው!
ናዳን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ፍሬያማ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ አሁን በባህርዳርና ዙሪያዋ ላይ በሚተገበረው ያ ጊዜ አሁን ነው! ፕሮጀክት በሁሉም የከተማችን ክፍለከተማዎችና ቀበሌዎች በርካታ ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ የዚህ አካል የሆነውን የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል፡፡ ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም የጀመረው ይህ ፕሮጀክት በሁሉም የከተማችን ቦታዎችና ዙሪያ ቀበሌዎች እስከ ህዳር 24/2015 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
...
ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት የባህርዳር ከተማ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፣ ስራና ስልጠና መምሪያ፣ የወጣትችና ስፖርት መምሪያ፣ የባህርዳር ከተማ ወጣቶች ማህበርና የስብዕና ማዕከላት ከእኛ ጋር በጋራ እየሰሩ ስለሆነ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ በከተማችን ታዋቂውና ለህዝባችን በጎ የአእምሮ እድገት የሚተጋው ዮፍታሔ መጻህፍት መደብር የዚህ ፕሮጀክት አጋዥና ተባባሪ በመሆንህ እናመሰግናለን፡፡





Comments
Post a Comment