ጥቂት ስለ መንደድ/መዛል/መታከት
ጥቂት ስለ መንደድ/መዛል/መታከት
በእንግሊዝኛው Burnout ተብሎ የሚጠራ ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ የሚችል የአካል፣ መንፈስና ስሜት መዝቀጥ ችግር ነው።
የስራ ላይ መሰላቸት ሲባል ብዙ ጊዜ ተቀጥረው ከሚሰሩ ሰራተኞች ጋር ይያያዛል። ይሁን እንጂ ይህ ችግር ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ የሚችልና ይህ ችግር የገጠመው ግለሰብ ከስራ ህይወቱ ባሻገር በማህበራዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ ማንነቱ ላይ ከፍተኛ መቃወስን የሚያስከትል ነው፡፡ ይህ ችግር የገጠመው ሰው ራሱን በመገምገም፣ በማነቃቃትና ሁኔታዎችን በማጤን ራሱን ከችግሩ ሊያወጣው ይችላል፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ እንዳሉት ጥናቶች ይህ ችግር የገጠማቸው ሰዎች ሁኔታዎችን ስለማይረዱና ችግሩ በውጫዊ ነገሮች ምክንያት እንደመጡ ስለሚያስቡ ራሳቸውን ከመገምገምና ከድባቴያቸው ከመውጣት ይልቅ ወደባሰ ውስብስብ ቀውስ ያመራሉ፡፡ ስለሆነም የስራ ወይም ህይወት ላይ መሰላቸት የገጠማቸው ግለሰቦች ልዩ ትኩረት የሚገባቸውና የስነልቦና ምክርና ክትትል እገዛ የሚሹ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የመንደድ ምልክቶች
👉ለስራ ሃይልና ስሜት ማጣት፣
👉ወደ ስራ ቦታ ሲሄዱ የመረበሽ፣ የመፍራት፣ ድብርት የመጫጫን ሁኔታ ውስጥ መግባትና ጥሩ ያልሆነ ነገርን መጠበቅ፣
👉ያሉበት ሁኔታ የስጋት እንደሆነ መሰማትና፣ ሰዎችን እንደ ተራ እቃዎችና ቁሶች መመልከት፣ 👉ዝቅተኛነት ስሜት፣
👉ያከናወኑትን ስራና የሚሰሩትን ስራ አፈጻጸም በአሉታዊ መልኩ የማየትና ውጤት አልባነት ስሜት እና መሰል አሉታዊ ስሜቶች ይሰማዎታል።
መታከት/የስራ ላይ መንደድ ሰዎች ያቀዷቸው ግቦች እንዳይሳኩና የተጠቂ ግለሰቡ አቅሙ እንዲወርድ ከማድረጉ በላይ ችግሩ በገጠመው ግለሰብ ላይ አስከፊ የአካላዊና አእምሮአዊ ችግሮችን ልክ እንደ ግፊት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ድብርት፣ ለአልኮልና ዕጽ ተጋላጭነት እና ሌሎች መሰል ችግሮችን ያስከትላል፡፡
ተቋማችን ናዳን ላለፉት ሶስት ዓመታት የባለሙያ መንደድ/መታከት ላይ ጥናቶችን በማካሄድ ለብዙ ግለሰቦችና ተቋማት የሰራተኞች መንደድን በማከምና በማስተዳደር ልምድን አግኝቷል። አሁንም በዚህ ችግር ለተጠቁ ግለሰቦችና ድርጅቶች ልዩ የመታከት/መንደድ መከላከያና ማከሚያ ፓኬጆችን በማዘጋጀት እየሰራን እንገኛለን፡፡
ይህንን ችግር ሲያቃልሉ
👉ግለሰቦች ጤናማ ማህበራዊ ህይወትን እንዲኖሩ፣ ውጤታማና ግብ የሚያሳኩ ይሆናሉ
👉በዚህ ችግር ምክንያት በተቋማት የሚመደበውን በጀት ከመክሰር ያድናሉ
👉ተቋማት በንቁ ሰራተኞች ራዕያቸውን ይደርሳሉ
Comments
Post a Comment